ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
26

የጨረታ ቁጥር 02/2018

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ እቃዎች ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ኤሌክትሮነክስ እቃዎች፣ ሎት 4 ፈርኒቸር የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፣ ሎት 5 የመኪና መለዋወጫና ዲኮር፣ ሎት 6 የመኪና ጎማ ከነ ከለመዳሪ፣ ሎት 7 የብስክሌት ጎማ ከነ ካለማደሪያ፣ ሎት 8 ህትመት (ላይት ቦክስ) ፣ ሎት 9 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አመታዊ ጥገና እንዲሁም ሎት 10 የእንጨትና ብረታ ብረት እቃዎች አመታዊ ጥገና  የመሳሰሉትን ግዥ ለመፈፀም በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የሚወዳደርበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ እና  የተጨሪ እሴት ታክስ  ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ የተጫራቾች መመሪያውንና የእቃዎችን ዝርዝር የሚገልጽ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሰራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 009 ባ/ዳር መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋው አንድ በመቶ ያላነሰ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ወይም ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ገቢ መደረግ ይኖርበታል፡፡
  4. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን በማስፈርና በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቬሎፕ ዋና እና ቅጅ ሰነዶችን ለየብቻ በማሸግ ለአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 013 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 የሚዘጋ ሲሆን በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የሚያግድ ነገር አይኖርም፡፡
  7. የርክክብ ቦታ ባ/ዳር ከተማ መ/ቤቱ ድረስ በግንባር በመቅረብ ይሆናል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ግዥዉ በቀረበዉ ዝርዝር መሰረት የእቃዉን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የአንዱ ዋጋ እና ጠ/ዋጋ መሞላት አለበት፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058 220 89 65 ደውሎ መረጃ መጠየቅ እና በተቋሙ ዌዩቭሳይት ANRSOAG.GOV.ET ባ/ዳር ማየት ይችላሉ፡፡

የአብከመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here