በማእከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለ በጀት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆኑ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- የሚወዳደሩት ዋጋው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 7 ዘወትር በስራ ስዓት ከጥቅምት 17/2018 እስከ ህዳር 01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ከህዳር 2/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡45 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በህዳር 02/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡46 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ በለለበት ሰነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ይከፈታል፤ ሆኖም ግን ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ ከመቤታችን የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከኦርጅናሉ የመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ በሌሉበት ሰነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ቅዳሜ ወይም ካላንደር ከሆነ በቀጣይ ቀን ጨረታዉ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ቅድመ ክፍያ መውሰድ የሚፈልግ ከሆነ በሚወስደው የቅድመ ክፍያ የገንዘብ መጠን ተመጣጣኝ የቅድመ ክፍያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡ ከዚህ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ዋስትና ተቀባይነት የለውም፡፡
- በጨረታ አሽናፊው ድርጅት የአሽነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ስነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከጽ/ቤቱ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 80 36 92 /09 18 29 44 21 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

