ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
33

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምሥራቅ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት/ በወረዳው ሥር ላሉ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛው በጀት ለሁሉም ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የአመታዊ ምድብ 1 የእስቴሽነሪ እቃዎች፣ ምድብ 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ምድብ 3 የስፖርት እቃዎች ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለሆነም መወዳደር ለምትፈልጉ ድርጅቶች  በሙሉ የጨረታ ሰነዱን በምሥራቅ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 በግንባር በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታድሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ የምዝገባ ሰርተፊኬት (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን 1.5 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው የሚገቡትን ውለታ በአግባቡ የሚፈጽሙ መሆን አለባቸው፡፡
  5. አሸናፊው ድርጅት ቅድሚያ ክፍያ የሚፈልግ ከሆነ እስከ 30 በመቶ የሚደርስ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
  7. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶችን በታሸገ ኢቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ተዘግቶ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፤ ድርጅቶቹና ወኪሎቻቸው ባይገኙም በየምድባቸው ቅደም ተከተል በአንድ ሰዓት ልዩነት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሞሉት ጥቅል ዝቅተኛ ድምር ዋጋ የሞላውን ድርጅት ነው፡፡
  10. ግዥ ፈጻሚ መ/ቤት በጨረታው የተጠየቀውን የእቃ መጠን እስከ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት ዋጋው ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  12. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  13. ጨረታዉ በሚከፈትበት ቀን በዓል /ካላንደር/ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. የቅሬታ ቀን ጨረታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 /አምስት/ የሥራ ቀናት ብቻ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  15. የታዘዙ እቃዎች በበጀት እጥረት ምክንያት አንሶ ሳይገዛ ቢቀር ጽ/ቤቱ የማይገደድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  16. መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ ምሥራቅ በለሳ ወረዳ ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 339 00 04 /01 16 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  18. ድርጅቱ ከፖስታዉ ላይ ከላይ ከተጠቀሱት መረጃዎች በተጨማሪ ማህተሙንና ፊርማዉን ማስቀመጥ አለበት፡፡
  19. እቃዎቹን እስከ ምሥራቅ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል መጋዝን ድረስ ማምጣት የሚችል፤ እንዲሁም መጫኛና ማዉረጃ በነጋዴዉ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

የምሥራቅ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here