ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
115

የጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ለጉና በጌምድር ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት እና በፕሮጀክት፣ በባዮ ጋዝ በጀት ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የኤሊክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የጽዳት እቃ፣ ሎት 4 የግንባታ እቃዎች፣ ሎት 5 ስሚንቶ፣ ሎት 6 የመኪና ባትሪ እና ጎማ እንዲሁም ሎት 7 የመኪና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡  በመሆኑም በዚህ የግልጽ ጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ፡-

በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ  ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

ይህ ግልጽ ጨረታ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ  15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ በጉና በጌምድር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17  በመምጣት ለእያንዳንዱ የማይመለስ 50.00 /አምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ጨረታ የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው  ቀን   ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ ጨረታውን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ ላይ ቢገኑም ባይገኙም ከመክፈት አያግድም፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ ዋስትና የምታስይዙት በቁርጥ  ለጽህፈት መሳሪያው 18,000.00 /አስራ ስምንት ሽህ ብር ብቻ/ ለግንባታ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 /ሃያ ሽህ ብር ብቻ/ ፣ ለስሚንቶ የጨረታ ማስከበሪያ 15,000.00 /አስራ አምስት ሽህ ብር ብቻ/ እንዲሁም ለኤሌክትሮኔክስ እቃዎች 8,000.00 /ስምንት ሽህ ብር ብቻ/ እንዲሁም ለፅዳት እቃዎች 1,500.00 /አንድ ሽህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ ፣የመኪና ባትሪ እና ጎማ 15,000.00 /አስራ አምስት ሽህ ብር ብቻ/ እንዲሁም የመኪና መለዋወጫ 12,000.00 /አስራ ሁለት ሽህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በጥሬ ገንዘብ  በመሂ-1 በማስቆረጥ በማስያዝ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ተጫራቾች በባንክ ያስያዙትን ማስረጃ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ጉ/በ/ወ/ገንዘብ ፅ/ቤት ብለው በመቁረጥ በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 17 ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16 ተኛው  ቀን 8፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ኦሪጅናል /ዋና/ በታሸገ ፖስታ ጉ/በ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡

አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5  የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከመ/ቤቱ ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን የውል ማስከበሪያ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ውል ካልወሰደ በግዥ መመሪያው 1/2003 መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡

የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

እቃው የሚቀርበው  /ርክክቡ የሚፈፀመው  በሙያተኛ ተረጋግጦ  ጉና በጌምድር ክምር ድንጋይ ከተማ በእየ ሴክተር መ/ቤቶች ባሉት ንብረት ክፍል ድረስ ነው፡፡

የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

የጨረታ አሸናፊው የሚለየው  በሎት መሰረት በሎት ድምር/ በጥቅል ድምር ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 24 86 86 /09 18 21 49 50 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጉና በጌምድ ገንዘብ ጽ/ቤቱ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here