የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4 ህትመት፣ ሎት 5 የህንፃ መሳሪያዎችና ብረታብረት ሎት 6 የከባድ ተሸከርካሪ መኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣ ሎት 7 በኤሌክትሪክ የሚሰራ የዕህል ወፍጮ ሎት 8 ፊኖ ዱቄት አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረበረ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ጠቅላላ ድምር ውጤት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ አንድ በመቶ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅ ፖስታዎች ማለትም፡- ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጥቅምት 17/2018 እስከ ህዳር 01/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሆነ ባይገኙም በሰዓቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ህዳር 02/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በሞባይል ቁጥር 09 18 73 44 61 /09 64 79 28 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ

