በደቡብ ወሎ ዞን የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተሁለደሬ ወረዳ ውሃና ኢ/ል ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ በጀት ሎት 1 የህንፃ መሳሪያ፣ ለተሁለደሬ ወረዳ ጤና ጥ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል በUNDP በጀት ሎት 2 የሀክምና መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩት ማስረጃዎች ጎላ ብለዉ መነበብ መቻል አለባቸው፡፡
- ጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከተሁለደሬ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለህንፃ መሳሪያ፡ ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ ለህክምና መሳሪያዎች ብር 20,000 /ሀያ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፖስታ ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ከጥቅምት 12/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 02/2018 ዓ.ም 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታዉ በህዳር 02/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ (ባይገኙም ይከፈታል) የጨረታ መክፈቻ ጊዜዉ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የሥራ ቀን የመክፈቻ ሰዓቱን ጠብቆ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው የሚለየዉ በሎት /በድምር/ ዋጋ ነዉ፡፡ በሰነዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዋጋ በሙሉ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ይሆናል፡፡ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠዉ ተጫራች መ/ቤቱ በጠየቀዉ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነፃፀር የተጋነነ ሆኖ ከተገኘ ጨረታዉ ዉድቅ ይሆናል፡፡
- ሁሉም የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸዉ፡፡ አሸናፊዉ ድርጅት እቃዎቹን ተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ወጭ አጓጉዞ በማቅረብ ንብረቱን በየንብረት ክፍሉ አስረክቦ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወስዳል፡
- ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለዉጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታዉ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም፡፡
- ጨረታዉን ለማዛባት የሞከረ ተጫራች ከጨረታዉ ዉጭ ሆኖ ወደፊትም በመንግስት ጨረታዎች አንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 222 00 12 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የተሁለደሬ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

