የፍ/ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ከወረቀት ነጻ የሆነ ህክምና ለመስጠት የፉል አዉቶ ሚሽን (ሙሉ ኔትወርኪግ) ሶፍት ዊር ለመግዛት ሶፍት ዊር አቅራቢዎችን በመጋበዝ በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የአንድ ጊዜ የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከታወቀ ሆስፒታል ላይ የፉል አዉቶሜሽን ሥራ ለመስራታቸዉ እና ከ 1 ዓመት በላይ ለመስራቱ የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ሶፍትዊር አቅራቢዎች ሶፍት ዌር ለመፍጠራቸዉ የባለቤትነት መብት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊዉ ክፍያ የሚከፈለዉ ሥራዉን ሰርቶ ካጠናቀቀ እና ሥራዉ በባለሞያ ከተረጋገጠ በኋላ በ2 ጊዜ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ መሰረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ሲሆን በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው ግዥዎች ለአንድም ግዥ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የፋይናንስ ቡድን ቢሮ በመሄድ ለሁሉም ሎቶች የመጫረቻ ሰነድ እያንዳንዳቸውን በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ እና አገልግሎት ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
- መሥሪያ ቤቱ 20 በመቶ ከግዥዉ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- መስርያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይም በፋክስ ቁጥር 058 775 13 32 እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058 775 00 16 /00 83 /10 16 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፍኖተ ሠላም ጠቅላላ ሆስፒታል


