ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
40

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉና በድጋሜ ለሚወጣዉ ለግንደወይን ከተማ መሰረተ ልማት ጽ/ቤት፤ በከተማዉ ለሚሰራዉ የአደባባይ ግንባታ ጨረታ መጫረት የምትፈልጉ የዘርፉ ተጫራቾች ለግንባታ ደረጃ 7 እና በላይ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2.ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4.የአገር ዉስጥ ፈርኒቸር፣ ሎት 5.ዘመናዊ ፈርኒቸር፣ ሎት 6.አደባባይ ግንባታ እንዲሁም ሎት 7.የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለማሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገዙ የእቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሎት 1 ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ የማይመለስ  ለሎት 2 እስከ 5 ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ለሎት 6 ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ የማይመለስ እና ሎት 7  ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ የማይመለስ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ረዳት ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር ለሎት 1 ብር 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 2 ብር 20,000/ሃያ ሽህ ብር/ ብቻ ለሎት 3 ብር 1,000 /አንድ ሽህ ብር/ ለሎት 4 ብር 3,000 /ሶስት ሽህ ብር/ ለሎት 5 ብር 1,400 /አንድ ሽህ አራት መቶ ብር/ ለሎት 6 ብር 150,000 /አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ ብር/ እንዲሁም ሎት 7 ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዝብ ገቢ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ግንደወይን ገ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ለግንባታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግንደወይን ገ/ጽ/ቤት /ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ከሎት 1-5 እና 7 ተኛዉ በ16 ተኛው ቀን  ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ እንዲሁም ሎት 6 የግንባታዉ በ22ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታው ያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ከተማ አስተዳደሩ ድረስ በራሱ ትራንስፓርት ወጭ ማቅረብ አለበት፡፡
  13. መ/ቤቱ የጨረታ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይለያል፡፡
  14. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ አቤቱታ (ቅሬታ) ካላቸው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውጭ የመጣ ቅሬታ ጽ/ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. መ/ቤቱ ከአሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን እቃዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. እቃዎችን በባለሙያ እየተረጋገጡ ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
  17. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  18. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መጥቶ ውል በመያዝ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  19. ከአሸናፊው ድርጅት 3 በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  20. ግዥ ፈፃሚው አካል ግዥውን ለመገምገም፣ ለማፅደቅ፣ አቤቱታ ቢነሳ ለማስተናገድ እና አሸናፊ ድርጅቱ ጋር ውል እስከሚገባ ድረስ የመጫረቻ ሰነዱ ጸንቶ የሚቆየበት ለ40 ቀን እና ለግንባታ ለ60 ቀን ይሆናል፡፡
  21. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በቁጥር 058 861 26 15 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡

የግንደወይን ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here