ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
39

በደቡብ ጎንደር ዞን የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ግን/አስ ቡድን በ2018 በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም 5 በጀት እና በመደበኛ በጀት ሎት 1 የፎቶ ግራፍና የእይታ መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የኤሌክትሪክ መሳሪያዎች (ተዛማጅ እቃዎች)፣ ሎት 3 የግብርናና የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 4 ፕላስቲክና የፕላስቲክ ውጤቶች፣ ሎት 5 አትክልትና ፍራፍሬ ዘር እንዲሁም ሎት 6 የደን የእፅዋት ዘር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች መሉ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን በድርጅቱ ስም የተዘጋጀ ማህተም መምታት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በሥራ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ1 ማስያዝ  ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኃላ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀን በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡
  11. ጨረታው በ16ኛው ቀን በ3፡00 ይታሸጋል፤ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 በዚሁ ቀን 3፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ጨረታውን ለመክፈት  ቢገኙም ባይገኙም አያስተጓጉልም፡፡
  12. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  13. ጨረታው የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
  14. በማስታወቂያ ያልተገለጹ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑ እና ለወደፊቱም በመንግስት ጨረታ አዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
  17. የጨረታ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደርያ ሃሳብ ላይ ለውጥ (ማሻሻያ) ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  18. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 2 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ 09 15 029 02 08 በመደውል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሰዴ ሙጃ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here