ግልጽ  የጨረታ ማስታወቂያ

0
78

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በእንጅባራ ከተማ የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ተጀምሮ ያልተጠናቀቀ የመጠጥ ዉሀ ፕሮጀክት ከፊል ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ በ2018 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት  ሎት 1. ባለ 100 ሜ/ኩብ የኮንክሪት ኮሌክሽን ቻምበር  (100m3 concrete collection chamber) እና የፓምፕና ጀኔሬተር ቤት ግንባታ ፣ሎት2. ለዉሀ ጉድጓዶችና ለቡስተር ጣቢያ የሚያገለግሉ የኦፕሬተር ቤቶች ፣የጥበቃ ቤቶች ፣የጀነሬተር ቤቶች ፣የአጥር ግንባታ እና የዉሀ ቦኖዎች ግንባታ በወጣዉ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር ቲን ሰርትፊኬት የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱ የሚዘጋጀው በአማርኛ ሆኖ የስራ ዝርዝሮች በእንግሊዘኛ ሊሆን ይችላል፡፡
  4. የተጫራቾች ደረጃ ለሎት1. ከ5 እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸው ፣ለሎት2. 9 እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  5. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የንግድ ፈቃድ ከፍሎ ያሳደሰን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ እና ከዚያ በላይ ከሆኑ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 2በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21/ሀያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት እንጅባራ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጀት ቢሮ ቁጥር 17 እስከ 11፡30 በማይመለስ  ለሎት 1. 1,000 /አንድ ሺህ/ ብር ፣ሎት 2   500/አምስት መቶ/ ብር መግዛት ይችላል፡፡
  9. የመወዳደሪያ ስርአቱ በሎት ዋጋ ነው፡፡
  10. የግንባታ ዝርዝሩን መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል፡፡
  11. የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ስም ማህተም አድራሻቸውን በጥንቃቂ  በታሸገው ፖስታ ላይ በትክክል በመጻፍ የቴክኒክና የፋይናንስ ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በመጨረሻም  በተጠቃለለ በአንድ ፖስት በማሸግ እንጅባራ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 17 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት  በ22 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ስአት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች የንግድ የስራ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች የአሸነፉባቸውን የግንባታ እቃዎች በራሳቸው ማስፈተሸ ወይም በማሰመርመር ማቅረብ  ግዴታ አለበቸው፡፡
  14. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
  15. በማንኛውም ምክንያት በሚመለከተው አካል ከጨረታ ውድድር ውጭ የተደረጉ (የታገዱ) ተጫራቾችን አያካተትም፡፡
  16. በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች ልዩልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚያድርጋቸውን ወቅታዊ የሆነ እና ለድርጅቱ በአድራሻ የተጻፈ ማስረጃ ማያያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ  ቁጥር 058 227 38 51 /0910418492/ በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here