ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
86

በደቡብ ጎንንደር ዞን የሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል በምድብ 1 የደንብ ልብስ፣ በምድብ 2 የእስቴሽነሪ እቃዎችን፣ በምድብ 3 ሌሎች አላቂ የቢሮ እቃዎችን ፣በምድብ 4 ህትመት ፣በምድብ 5 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ፣በምድብ 6 የፈርኒቸር እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ማስረጃ የሚያቀርቡ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የእቃዎችን ዝርዝሩ መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከረዳት ገንዘብ ያዥ ክፍል ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ናሙናዎቹን ከዚሁ ክፍል ማየት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለዉድድር ያስቀመጡትን ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ያስያዙትንም (ሲፒኦ) ወይም የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡንና ማስረጃዎችን ዋናዉን በጥንቃቄ በታሸገ በአንድ ፖስታ ለሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ተብሎ ተጽፎበት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 16ኛዉ ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የሚታሽገውም በዚሁ ሰዓት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በገንዘብ ጽ/ቤት በ16ኛዉ ቀን 4፡00 በጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴ ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊዉ ማሸነፉ ከተገለጸለት ከ5 ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ዉስጥ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን ልክ የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ዉል መዉሰድ ያለበት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ዉል ካልወሰደ በግዥ መመሪያዉ መሰረት አስፈላጊዉን እርምጃ ይወሰዳል፡፡
  11. የሚቀርቡ አቅርቦቶች የሚያቀርበዉና ርክክብ የሚፈጸመዉ ጥራቱ ከተረጋገጠ በኋላ በሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ሃሙሲት ከተማ ላይ ይሆናል፡፡
  12. የጨረታ መክፈቻዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል፡፡
  13. የጨረታ አሸናፊዉ የሚለየዉ ለሁሉም ዕቃዎች በሰጠዉ ጥቅል ዋጋ ድምር የሚወስን ሲሆን በሰነዱ የዋጋ መሙያ ቦታ ላይ የአንዱንም እቃ ዋጋ ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  15. ስለጨረታዉ ዘርዝር መረጃና ማብራሪያ ከፈለጉ ሃሙሲት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 443 03 20 /04 00 /09 18 53 10 53 ደዉለዉ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ ፡፡

የሃሙሲት ከተማ አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here