ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
12

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደባይጥላት ግን ወረዳ የቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጀ ቤት በ2018 የበጀት አመት በከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት የማሽን ክራይ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለመንገድ ግንባታ የሚያስፈልገው ማቴሪያል ወይም ጠጠር የሚመረትበትን ቦታ ማዘጋጃ ቤቱ የሚያሳይ ሲሆን በጥራት የሚሰራ ሆኖ ከተጫራቾች መካከል አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ የማሽን ፈቃድ ያላቸው አካላት ማጫረት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የማሽን ኪራይ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የሞሉት ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በወጣው የሥራ ዝርዝር መሰረት ሁሉንም ወጭ የሚችሉ ማለትም ለመንገድ ሚያስፈልገውን ነዳጅ እና የማሽኖችን ማምጫና መውሰጃ (ሎቨድ) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል በቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ሁኖ የጠቅላላ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ ከ5 በመቶ ያላነሰ እና ከ2 በመቶ ያልበለጠ የገንዘብ መጠን በጨረታው ሰነድ ወስጥ መገለጽ አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቁይ መሪ ማዘጋጃ ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ስማቸዉን ማንነታቸዉን የሚገልጽ መሉ አድራሻቸዉን እና የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  9. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. የማሽን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆይበት ለ21 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም በሮ ቁጥር 07 ጋዜጣው በወጣ 22 ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 4፡00 ላይ የሚከፈት ሲሆን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ባወጡት ወጭ መሥሪያ ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡
  14. በውድድሩ የተገኘዉ ዋጋ ሳይቀየር መሥሪያ ቤቱ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡
  16. አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ (ሎት) ሞልቶ ካቀረበ ይሆናል፡፡
  17. አሸናፊው ተጫራች ወይም ድርጅት ለመንገድ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ማቴሪያል ወይም ቁሳቀስ ትራንስፖርት ቦታው ድረስ እራሱ የሚያጓጉዝ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  18. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል መያዝ አለበት፡፡
  19. ተጫራቾች የጨረታውን መጠን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  20. ሥርዝ ድልዝ ካለው ልዩ ፊርማ መቀመጥ አለበት፡፡ ልዩ ፊርማ ከሌለው ተቀባይነት የለውም፡፡
  21. አድራሻችን በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደባይ ጥላን ግን ወረዳ ቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ከአዲስ አበባ 284 ኪ/ሜትር ከባሕር ዳር 324 ኪ/ሜትር ከደብረ ማርቆ እስከ ቁይ 60 ኪ/ሜትር ላይ ትገኛለች፡፡
  22. ለተጨማሪ መረጃ 09 62 78 65 91 /09 20 50 69 44 መደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-ነዳጅ እና የማሽኖች ማምጫና መውሰጃ (ሎቤድ) ተጫራቹ የሚችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ (ሲፒኦ) ማስያዝ የሚቻለዉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአቢሲንያ ባንክ ቡና ባንክ፣ ዓባይ ባንክ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የቁይ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here