የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የማዋለጃ ክፍል ሴራሚክ ማንጠፍ እና ሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ያሉ ህንፃዎችን የውስጥ እና የውጭ ቀለም ቅብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ይህንን ሥራ ለማሰራት ከደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሥራዎችን ለመስራት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሥራው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ሥራዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው መሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማረኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
- በዚህ ጨረታ መጫረት የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 30 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሽጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ31ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድ ቅዳሜና በአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተጠየቀው ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራች አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚመለስ ለእያንዳንዱ ብር 4,000 /አራት ሽህ ብር/ ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የማዋለጃ ክፍል ሴራሚክ ማንጠፍ እና የሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ያሉ ህንፃዎችን የውስጥ እና የውጭ ቀለም ቅብ ለሥራው የሚያስፈልጉ ሁሉንም ማቴሪያሎች ሆስፒታሉ የሚችል ሲሆን ለመስሪያ የሚሆን ተጫራቹ የሚችል ሆኖ እና በመስሪያ ቤቱ ፕላን ወይም ዲዛይን (ስፔስፊኬሽን) መስረት ሰርቶ የሚያስረክብ እና በሆስፒታሉ ውል ይዞ ሊሰራ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አንድ ተጫራች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውን ላወጣው መሥሪያ ቤት በፅሁፍ ወይም በፋክስ ቁጥር 058 661 02 64 እንዲሁም በስልክ ቁጥር 058 661 03 30 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡ ጨረታውን ያወጣው መሥሪያ ቤት የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል

