ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
30

የአዊ ብሄ/አስ ዞን የቻግኒ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የገቢ ግዥ ፋይ/ን/አስ/የስራ ሂደት በ2018 በጀት አመት የፋይናንስና የንብረት እንቅስቃሴ ስራ ኦዲት አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ እና ሶላርና የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች አቅርቦት ግዥ ለመግዛት ስለሚፈለግ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. ማንኛውም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከ200ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ፎቶ ኮፒ አያይዘው የሚያቀርቡ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል የቻግኒ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 4 ሰነዱን በመግዛት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  5. የማወዳደሪያ ስርዓቱ በጥቅል ነው፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን መሂ-1 የሞሉትን ዋጋ ሁለት በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቻግኒ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት የገቢ ግዥ ፋይ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ማስታወቂያው ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀናት እስከ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ቻግኒ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. የኦዲት አገልግሎት ጨረታ በቴክኒካል ዉጤት 70 በመቶ እና በላይ ያገኙ ተጫራቾች ብቻ ለዋጋ ዉድድር እንዲያገኙ ጥሪ ይደረግላቸዋል፡፡ በቴክኒክ መስፈርቱ ከ70 በመቶ በታች ያገኙ ተወዳዳሪዎች የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ ሳይከፈት ይመለስላቸዋል፡፡
  10. ስርዝድልዝ ያለው የዋጋ አሞላል ተቀባይነት የለውም፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ለጨረታ መወዳደሪያ ሃሣብ ማቅረቢያ ከተወሰነ ጊዜ ገደብ ከ5 ቀን በፊት ማቅረብ ይችላሉ፡
  12. አሸናፊዉ አካል ለውል ማስከበሪያ 10በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን መሂ-1 ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  13. አሸናፊ የሆነው ድርጅት በራሳቸው ወጪ እስከ ቻግኒ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ት ድርጅት ድረስ በማምጣትና በባለሙያ በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡ ኦዲት የሚመረመረው ቻግኒ ድረስ በመምጣት ነው፡፡
  14. የተያዘው የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ድርጅቱ ውል እንደተያዘ ለተሸናፊዎች ተመላሽ ይሆናል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ ከቻ/ከ/ውሃና ፋሳሽ አገ/ት ድርጅት የገቢ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁ.-4 ድርስ በአካል ወይም በስ.ቁ 058 225 09 04/02 22/00 33 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቻግኒ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here