ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃ፣ ሎት 3 የመኪና እቃ የመደበኛ፣ ሎት 4 የመኪና እቃ የፕሮጀክት፣ ሎት 5 የመኪና እቃ ጥገና የመደበኛ እና ሎት 6 የመኪና እቃ ጥገና የፕሮጀክት ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የቫት እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. በአዲሱ የንግድ ፈቃድ መሠረት ንግድ ፈቃድ ያወጡ፡፡
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢነት ሠርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
  6. ለመኪና ጥገና ተጫራቾች ደረጃ 2፣3 እና በላይ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  8. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ድረስ ሠነዱን የማይመለስ ለአንድ ሎት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በኮ/እ/በ/ቅ/ጥ/ም/ላብራቶሪ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃ አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ እና ለመኪና ጥገና 3 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማሲያዝ አለባቸዉ፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለኮ/እ/በ/ቅ/ጥ/ም/ላብራቶሪ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ጨረታዉ ተጫራቾች ባሉበት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በኮ/እ/በ/ቅ/ጥ/ም/ላብራቶሪ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 ከጥቅምት 24/2018 – ህዳር 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተቆጥሮ በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ተዘግቶ በዚያዉ ቀን 4፡30 ላይ የሚከፈት ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን በዚያዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. ለመኪና ጥገና አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ለአንድ አመት ውል ገብቶ መስራት የሚችል፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  15. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 351 88 43 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here