ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
15

የደብረ ታቦር አጠቃላይ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ የጽዳት እቃዎችን፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ  ጥገና፣ የዉሃ ቧንቧ መለዋወጫ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎችን የተለያዩ ህትመቶችን፣ የሙያተኞች የፕላስቲክ ዶክተር ሹዝ ጫማ የጥገና እቃዎች፤ የተለያዩ ብትን ጨርቆች ለሙያተኞችና ለበሽተኞች አገልግሎት የሚውሉ፤ የመብራት መለዋወጫ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች እና ሊድ ሽልድ ባለ ጎማ (ተንቀሳቃሽ የሆነ) ከሊድ ግላስ ጋር ለማሰራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዝቅተኛ ዋጋ ከሞሉ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ (የሥራ) ፈቃድ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያለቸዉና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃዎች (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኙታል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚፈለግባቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዉን በጀርባዉ ላይ ከዋናዉ ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍና ማህተም፣ ስም፣ ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ከግ/ፋ/ን/አስ//ቡድን ቢሮ ዉስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ 1 በመክፈል ማስያዝና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም (በሲፒኦ) ከሆነ ዋናዉ (ሲፒኦ) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራቾች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት በአንድ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመፃፍ በደ/ታቦር ሆስፒታል ውስጥ ከግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን  ቢሮ ውስጥ  በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሠዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ  ቀናት የሚውል ሲሆን ፖስታውን እስከተገለፀው ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በ16ኛው ቀን ጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሁሉም  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት  በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን የበዓል እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸዉ እንደተገለፀላቸዉ ቅሬታ ከማቅረቢያ ጊዜ በተጨማሪ ባለዉ አምስት /5/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ሆስፒታሉ ድረስ በመምጣት ዉል መዉሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  12. አሸናፊዎች የዉል ማስከበሪያ አስር በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  13. አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዕቃ በራሳቸው ወጭ ሆስፒታሉ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. ተጫራቾች ለውድድር ከቀረቡ በኃላ ሀሣባቸውን መለወጥ (ማሻሻል) ወይም እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  15. ተጫራቾች ሆስፒታሉ አስፈላጊ ሁኖ ካገኝ አሸናፊውን በጥቅል ድምር ሆነ በተናጥል ይለያል፡፡ ነገር ግን በጥቅል ለመለየት የማይገደድ ይሆናል፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  1. ለበለጠ መረጃ ከግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር 058 441 16 57 /09 20 44 22 25 /09 18 19 51 75 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደብረ ታቦር አጠቃላይ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here