ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
16

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምዕራብ በበለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓ/ም  በወረዳው ውስጥ  ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች  አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እና ሎት 2 የኤሎክትሮኒክስ  እቃችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት  ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- በጨረታው ለመወዳደር  መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት)ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የሚገዙ እቃዎችን አይነት እና ዝርዝር በተመለከተ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ም/በ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 10 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጥቅምት 24/2018 ዓ/ም አስከ ህዳር 08/2018 ዓ/ም 11፡30 ድረስ ቆይቶ በህዳር 09/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ ካለው ከፊት ለፊቱ ልዩ ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች ለሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመ/ቤታችን ባሉ ረዳት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) አልያም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ምዕ/በ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ገንዘቡን ለረዳት ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኙን ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ሁሉም እቃዎች በጥራት ኮሚቴ ትክክለኛነታቸውን ሲረጋገጥ ገቢ ይደረጋሉ፡፡
  12. ጨረታው በክልሉ ገ/ኢ/ል/ቢሮ ባወጣው የግዥ መመሪያ የሚተዳዳር ይሆናል
  13. ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 70 11 12 04 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የማዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ በለሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here