ለእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 3 ህትመት እና ሎት 4 እድሳት እና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ወይም ተቋሙን ማሳደስ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መወዳደር ለምትፈልጉ መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ግዥ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርገው እብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ሆስፒታሉ የሚገዛቸውን እቃዎች ወይም እድሳት እና ጥገና 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡትን እቃዎች ወይም እድሳት እና ጥገና ዝርዝሩን ሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው፤ አንድም እቃ አለመሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ወይም የእድሳት እና ጥገና አይነት (ስፔስፊኬሽን) መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
- ሆስፒታሉ አሸናፊውን በጥቅል ዋጋ ይመርጣል፡፡
- ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ቢገኙም ባይገኙም በ16ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በ8፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፋቸውን እቃዎች እብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል፡፡
- በሎት 4 ላይ የተጠቀሰው እድሳት እና ጥገና ተጫራቾች ሙሉ ማቴሪያሉን ራሳቸው በማቅረብ መስራት የሚችሉ እና ደረጃቸው ከደረጃ 7 በላይ መሆን አለበት፡፡
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስትሞሉ ሥርዝ ድልዝ (በፍሉድ) የጠፋ መኖር የለበትም
- አሸናፊው ተጫራች በስሙ የታተመ ህጋዊ ደረሰኝ ያለው መሆን አለበት፡፡
- ደረቅ ቸክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
- አሸናፊው ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ውል መውሰድ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በተለያያ ምክንያት የጨረታ ሰነዱ ችግር ቢኖርበት ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስተካከያ የሚደረግበት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለማሸነፍ ሲባል የተወሰኑትን እቃዎች በጣም በዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ አላቀርብም (ገበያ ላይ የለም) ማለት አይቻልም፡፡
- በዚህ ሰነድ ያልተገለፀ ሀሳብ ቢኖር በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 440 09 13 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የእብናት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

