በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሥራ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ መሂ 1 በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 01/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 15/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 15 ቀናት ይቆያል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ህዳር 16/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ፣ ፍቀት እንዲታይበት አይፈቀደም፡፡ ሆኖም እንዳጋጣሚ ሥርዝ ድልዝና ፍቀት ቢታይበት በፊርማ /ፓራፍ/ መረጋገጥ አለበት፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን ህዳር 16/2018 ዓ/ም በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- የሚገዙት እቃዎች የማስረከቢያ ቦታ ወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው የሚለየው በሎት ድምር ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 118 05 21 ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

