ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
38

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት በመደበኛ ካፒታል በጀት በሙሉ ዋጋ በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ በደረጃ 9 /ዘጠኝ/ እና በላይ በጉንኮ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት፣ በዳብር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እና በአንጅባ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተለውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የሥራ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የንግድ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. የግዥ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 ተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚገነቡት ግንባታዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5 መቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጽ/ቤቱ መሂ 1 በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከህዳር 01/2018 ዓ/ም እስከ ህዳር 21/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 21 ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ህዳር 22/2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን ህዳር 22/2018 ዓ/ም በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ  ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 118 05 21 ወይም ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመገኘት  ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እና በተጨማሪም ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን በተጫራቾች መመሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የወገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here