በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በደ/ታቦር ከተማ አስተዳደር ላሉ ተቋማት የጽህፈት መሳሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ በተጠቀሰው የጨረታ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ያቀረበው ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ማቴሪያሎችን ዝርዝር መግለጫ (ሰፔስፊሌሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሚወዳደሩበት የዕቃዎች ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም ደብር ታቦር ከተማ አስ/ገን መምሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሥርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቾችን ሥም፣ ፊርማና ማህተም ጨረታውን ያወጣው መ/ቤት ስምና አድራሻ በመግለጽ በደ/ታ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ባሉት ቀናት ማስገባት ይኖርባቸል፡፡
- ጨረታው ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡10 ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትብት እለት በዓል ቀን ከሆነ የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ሰዓቱን ጠብቆ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከነጠላም ዋጋ ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በተጫራቾች ላይ የሚሞላ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ቢሆንም ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
- በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ (ተመስርቶ) መጫረት አይችልም፡፡
- የጨረታ መዝገጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ውድድሩ በሎት ስለሆነ አንደም እቃ ሳይሟላ መቅረብ የለበትም ሳያሟላ ከተገኘ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
- የእቃው መጠን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- መምሪያው በጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የመረጠውን ዓይንት የመግዛት መብት አለው፡፡
- እቃው የሚቀርብበት ቦታ ደብረታቦር ከተማ ገንዘብ መምሪያ ድረስ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ/ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 02 09 /058 141 93 75 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ታቦር ከተማ አስስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

