ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
120

የደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 ዓ/ም የተለያዩ የማሰልጠኛ እና ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ እቃዎችን ማለትም ሎት 1 የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 2 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 3 የግብርና እቃዎች፣ ሎት 4 የኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5 የአውቶ እቃዎች፣  ሎት 6 የጋርመንት እቃዎች፣ ሎት 7 ብትን ጨርቅ እንዲሁም ሎት 8 ጫማ እና የተዘጋጁ ልብሶች ሲሆኑ ሁሉም ውድድሮች በሎት የሆነ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-

በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡

ከመንግስት የሚጠበቅበትን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው ማስረጃውን አያይዛችሁ ማቅረብ የምትችሉ፡፡

ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን  ጀምሮ በደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነት የማይመለስ 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈልና በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን በ16ኛው ቀን በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም የመክፈቻ ጊዜው አይራዘምም በዚህ እለት ህዝባዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡

በጨረታ ሰነዱ ላይ የተወዳዳሪው የድርጅቱ ማህተም፣ ስምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻ ማስቀመጥ ይኖርባችኃል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን እቃ ኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ማሸነፋቸው እንደተገለጸላቸው በ5 ቀን ውስጥ ውል ከኮሌጁ ጋር መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም፡፡

የጨረታውን አሸናፊ የምንለየው በሎት /ድምር/ የሚታይ ስለሆነ ተጫራቾች ሁሉንም አይተሞች መሙላት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሁሉንም ማቴሪያሎች ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡

ኮሌጁ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 117 08 06 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

የደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here