የጎንጅ ቆለላ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ ቡድን በ2018 በጀት አመት አገልግሎት ለሚሰጣቸው መ/ቤቶች ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች (ለባህል ቡድኖች የሚያገለግል)፣ ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 5 የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ ሎት 6 ስሚንቶ፣ ሎት 7 የህትመት አገልግሎት፣ ሎት 8 የመኪና ጎማ እና ሎት 9 የመኪና መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምትሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የእቃዉን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ጎንጅ ቆለላ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥዉ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ድርጅት አሸናፊቱን ከተገለፁ በኋላ የዉል ማስከበሪያ የጠቅላላዉን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከህዳር 01/2018 እስከ ህዳር 16/2018 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ህዳር 16/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ህዳር 16/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብና /ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 556 75 58 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት፡፡ ሆኖም ሥርዝ ድልዝ ካለ ስለ መስተካከሉ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ 20 በመቶ መጨመር (መቀነስ) ይችላል እንዲሁም ማንኛውም ተጫራች ግዥ ንብ/አስ/ ቡድን ሳምፕል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን እቃውን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት ፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሰ በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

