ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
66

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ 1. የጽህፈት መሳሪያዎች፣ 2. ኤሌክተሮኒክስ ዕቃዎች፣ 3. የጽዳት ዕቃዎች 4. ኢምፖርትድ ፈርኒቸር እና 5. የስፖርት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ  ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ከአዊ ብሄ አስ/ዞን የእን/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጨረታው በወጣበት 16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 08 ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር የሚጫረቱትን አንድ በመቶ (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ (በመ/ቤቱ መሂ 1 ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. የውድድሩ ሁኔታ በየሎቱ በሎት ዋጋ ድምር ነው፡፡
  8. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 227 12 58 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here