በምሥራቅ ጎጃም ዞን የደብረ ወርቅ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚዉሉ በሎት 1 የተለያዩ መጠን ያላቸዉ የዉሃ መስመር መገጣጠሚያዎች ግዥ (HDPE እና GS) መገጣጠሚያዎች እና በሎት 2 ኮምፒዉተር ከነ ሙሉ አክሰሰሪዉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መመዘኛዎችን አሟልተዉ ከተገኙ መጫረት ይችላሉ፡፡
- የከፈሉበትን የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃዎችን አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለጨረታዉ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ተዕዛዝ ወይም (ሲፒኦ) ማስያዝ የሚችሉ ሆኖ አሸናፊ ከተለየ በኋላ ለአሸናፊነት ላልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸናፊዉ ጋር ዉል ከተያዘ በኋላ ይመልስላቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ስምና አድራሻቸዉን በኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ ላይ በትክክል በመፃፍና በስም በማሸግ በደ/ወርቅ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ድርጅት የገ/ግ/ፋ/ን/አስ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡
- ጽ/ቤቱ ተጫራቾችን በሚያወዳድርበት ጊዜ በጥቅል ዋጋ ያወዳድራል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፤ ቫትን ሳይጨምር የሞላ ወይም ከቫት ጋር መሆኑንና አለመሆኑን የሚያጠራጥር ከሆነ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም ስለእርማቱ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱን በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ በ 5 የሥራ ቀናት ዉስጥ የዋጋዉን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በማቅረብ ድርጅቱ ድረስ በመቅረብ ዉል መፈረም አለበት፡፡ ዉል ሳይፈርም እቃዉን ይዞ የመጣ አሸናፊ ለሚፈጠረዉ መጉላላትና ችግር ድርጅቱ ተጠያቂ አይደለም፡፡
- አሸናፊዉ ወይም ተወዳዳሪዉ በተጠቀሰዉ ጊዜ ገደብ ዉስጥ ቅድመ ሁኔታዉን አሟልቶ በመቅረብ ዉል ካልያዘ ጨረታዉን በፈቃዱ እንደሰረዘ ተቆጥሮ ያስያዘዉ የጨረታ ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ማንኛዉም ተወዳዳሪ የእቃዎችን በሰነዱ ላይ ያለዉን ስፔስፊኬሽንና ዝርዝር መግለጫዎች በሚገባ በመገንዘብ መሙላት ይኖርበታል፡፡ የስፔስፊኬሽን ችግር አለበት ብሎ ያሰበ ተወዳዳሪ ጨረታዉን ከመሙላቱ በፊት በጽ/ቤቱ ስልክ ቁጥር 09 20 05 49 01 /09 18 47 25 67 በመጠየቅ መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉን ሞልቶ አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ ለሚቀርብ የስፔስፊኬሽን ችግር ተቀባይነት የለዉም፡፡
- አሸናፊዉ ያሸነፋቸዉን እያንዳንዱ እቃዎች በስፔስፊኬሽኑ መሰረት በራሱ ወጭ መ/ቤቱ ድረስ የማቅረብ ግዴታ ይኖረበታል፡፡ የሚቀርቡ እቃዎች በባለሙያ እየታዩ የጥራት ችግር ካለባቸዉ ጽ/ቤቱ ለመረከብ አይገደድም፡፡ በተያዘዉ ጊዜ ዉስጥ የማያቀርብ ከሆነ ያስያዘዉ 10 በመቶ በሙሉ ወደ ጽ/ቤቱ ገቢ የሚደረግ ይሆናል፡፡
- የጨረታዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከህዳር 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ቆይቶ በ16 ኛዉ ቀን 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎች ባሉበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ በዚያን ዕለት ካሌንደር የሚዘጋ ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታዉ ከተዘጋ በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም፡፡
- ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ በማንኛዉም ሁኔታ ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ የተሰጠዉን ዋጋ መለወጥ አይችሉም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 663 05 22 /09 20 05 49 01 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደብረ ወርቅ ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

