ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
49

የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግቢው ውስጥ የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለህጋዊ ነጋዴዎች መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና ጠቅላላ ዋጋው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ መቆያ ጊዜ ከህዳር 1/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 15/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ሲሆን ተጫራቾች ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከህዳር 1/2018 ዓ.ም አስከ ህዳር 15/2018 ዓ.ም እስከ 11፡30 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተወዳዳሪዎች ብር 20,000 /ሀያ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ህዳር 16/2018 አ.ም ጠዋት 3፡30 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን 3፡45 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ለመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
  7. የመክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊው ማሸነፋ በተገለጸ ከአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በኃላ ባሉት አምስት የሥራ ቀናት ውሥጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 774 07 71 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ መረዳት ይችላሉ፡፡
  10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  11. ሌሎች በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዩች ካሉ በግዥ መመሪያ የምንገዛ ይሆናል፡፡
  12. የማስመዘኛና የማስጫኛ ወጭዎች በአሸናፊ ድርጅቶች የሚሸፈን ይሆናል፡፡

ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here