የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ማለትም፡- ሎት 1. የማገዶ እንጨት፣ ሎት 2. የኤሌክትሪክ መሳሪያዎችና ተዛማጅ እቃዎች እንዲሁም ሎት 3. የኮምማውተር መሳሪያዎችና ተጓዳኝ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
- የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም የእቃ ግዥ ከብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ እና ለአገልግሎት ከ10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ 3 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
- የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኙት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ (በሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 10 በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና (ቲን) በአንድ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ ት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ማለትም ህዳር 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ነገር ግን ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በሎት የጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን ምርቱን (እቃውን) በራሱ የትራንስፖርት ወጭ በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
- አድራሻ፡- ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ 09 20 50 43 80 /09 20 50 68 87 /09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

