የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 ጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት 3 የቢሮ መገልገያ፣ ሎት 4 ፈርኒቸር፣ ሎት 5 የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት 6 የጽዳት እቃ፣ ሎት 7 ህትመት፣ ሎት 8 የፋብሪካ ማቴሪያል፣ ሎት 9 የመኪና ጎማ እና ሎት 10 የመኪና ሰፔርፓርት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸዉ አቅራቢዎች በሎት አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና 2017 ዓ.ም የስራ ግብር ሙሉ በሙሉ ከፍሎ ያጠናቀቀ መሆን ይኖርበታል፡፡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር አንድ በመቶ የጨረታ ሳጥኑን ከመከፈቱ ቀድሞ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን የእቃ ዋጋ 10 በመቶ ወድያዉኑ (ሲፒኦ) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ዉል በመዉሰድ የተጠየቀዉን እቃ ጥራት ጠብቆ በኦሪጅናል ሊያቀርብ ይገባል፡፡
- ያሸነፉበትን እቃ ለማቅረብ ዉል የማይወሰድ ወይም ዉል ከወሰደ በኋላ እቃዉን የማያቀርብ ተጫራች ቢያጋጥም መ/ቤቱ ለዉል ማስከበሪያ የያዘዉን (ሲፒኦ) ወይም ጥሬ ገንዘብ መዉረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ 1 ዓመት ለሚደረስ ጊዜ በጨረታ እንዳይሳተፍ የማገድ ስልጣኑን ለመጠቀም ይገደዳል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የማወዳደሪያ ዋጋ ሲሞላ ሁለት ኦርጅናል በሁለት ፓስታ ታሽጎ ማስገባት ሲኖርበት ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ከጨረታዉ እንድሰረዝ ይደረጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ሳጥኑ መግባት ያለበት ኦርጅልናል እና ኮፒ ሆኖ በሁለት ፖስታ ታሽጎ ከፖስታዉ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ ተጽፎ ከሳጥኑ ዉስጥ ሊገባ ይችላል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይችላል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የንግድ ፈቃዱን የማይመለስ 1 ኮፒ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ 1 ኮፒ፣ ቫት (ቲኦቲ) የምስክር ወረቀት የማይመለስ 1 ኮፒ በፖስታ ዉስጥ በማሸግ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ለሚያቀርበዉ እቃ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ሊኖረዉ ይገባል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ታስቦ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ የመ/ሰ/ከ/ገ//ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 210 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታዉ በዚሁ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሲሆን ታሽጎ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸዉ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የሚቀርበዉ እቃ በተጠየቀዉ (ስፔስፊኬሽን) መሰረት መሆን ይጠበቅበታል፡፡
- የሚቀርበዉ እቃ በኦሪጅናል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታዉ ያሸነፈዉ ግለሰብ የሚያቀረበዉን እቃ መካነ ሰላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤቱ ድረስ የሚያመጣዉ በራሱ ወጭ መሆኑ ይታወቅ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በሎት ድምር ስለሆነ በጥንቃቄ ሊሞሉ ይገባል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
መካነ-ሰላም ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤቱ

