ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
53

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የደንብ ልብስ፣ ሎት 2. የመኪና ጎማ፣ ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 4.የጽዳት እቃ፣ ሎት 5 የህትመት ውጤቶች፣ ሎት 6 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 7 ህንፃ መሳሪያ፣ ሎት 8 ፈርኒቸር፣ ሎት 9 የመኪና መለዋወጫ እቃ፣ ሎት 10 ደንብ ልብስ ስፌት አቅርቦት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡- የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ በተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሡትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ጥሬ ገንዘብ ከፖስታ በማስገባት ወይም ከሆስፒታሉ ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ ከፖስታው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  6. የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት በመቶ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዱ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ከላይ በሎት የወጡት የጨረታ አይነቶች ጋዜጣዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለ15 ቀን በስራ ስዓት እስከ 11፡30 ድረስ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በ16ኛ ቀን 4፡00 ድረስ የገዙትን ሰነድ አስገብተው 4፡10 ላይ ይከፈታል፡፡
  9. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን በስዓቱ ካልተገኙ ሆስፒታሉ በሌሉበት የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሆስፒታሉ ግ/ፋ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጥንቃቄ ያልታሸገ ፖስታ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
  11. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  12. አሸናፊ ተጫራች የአሸነፈውን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አምደወርቅ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡ ከታዘዘው ስፔስፊኬሽን ውጭ ቢያቀርብ በራሱ ወጭ እቃውን ወስዶ ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፡፡
  13. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ጨረታው ሥርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  15. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
  16. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በሆስፒታሉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በቢሮ ስልክ ቁጥር 033 461 13 48 /09 13 80 53 99 /09 29 42 29 92 በመደወል የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here