ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

በምሥራቅ ጐጃም ዞን የማቻከል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በወረዳ ወስጥ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ማለትም ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2 የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣ ሎት 3 ኮምፒውተር እና ተዛማጅ እቃዎች፣ ሎት 4 ዉጭ ፈርኒቸር፣ ሎት 5 የሀገር ዉስጥ በፈርኒቸር ለማሰራት እንዲሁም ሎት 6 ያገለገሉ ብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን በማቻከል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የተዘጋጀውን የዕቃን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም በዋጋ መሙያው ላይ ስርዝ ድልዝ በግልጽ የማይነበብ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ያቀረበ ከዉድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  4. ሰነዱን በጥንቃቄ ሞልቶ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን አድራሻ፣ ህጋዊ ማህተም ሙሉ ስምና ፊርማ በመፃፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን ጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የእቃ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ተራ ቁጥር 1 ፣2 እና 3 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ተራ ቁጥር 4፣6 ብር 10,000 /አስር ሽህ ብር/ እና ተራ ቁጥር 5 ብር 5,000 /አምስት ሽህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ውድድሩ በምድብ ሎት በጥቅል ድምር ዋጋ የእያንዳንዱ ሎት አሸናፊ የሚለይ ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል አንዱንም እቃ ሳይሞላ ቢቀር ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  8. መ/ቤቱ በውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ የማለት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ተጫራቾች በሚፈጥሩት ስህተት ለሚከሰተዉ የገንዘብም ሆነ የጉልበት ኪሳራ ጽ/ቤቱ ከላይ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  10. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው አይነትና (ስፔስፊኬሽን) መሰረት በትክክል ተሞልቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. አሽናፊ ተጫራቾች የአሽነፋበትን እቃ ከተማው ውስጥ ባሉት ሴ/መቤቶች ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
  12. ጨረታው በ16 ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡00 ያክፈታል፡፡ በዚሁ እለት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኘም ባይገኙም በግልጽ ይከፈታል፡፡
  13. አሸናፊ ድርጅቱ በወረዳ በሚገኘዉ ፍትህ ጽ/ቤትት ዉል መያዝ ይኖርበታል፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 777 04 80 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የማቻከል ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here