የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በመ/ቤቱ ላሉ የሥራ ሂደቶች፣ ለአዘዞና ለጠዳ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ እቃዎችና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ሎት 01 የደንብ ልብስ፣ ሎት 02 ከጥጥ የተሰራ ካፖርት፣ ሸሚዝ፣ የዝናብ ልብስና ጥላ፣ ሎት 03 የአገር ውስጥ የሴትና የወንድ አጭር ቆዳ ጫማና ፕላስቲክ ቦት ጫማ፣ ሎት 04 የጽህፈት መሳሪያዎች (አላቂ የቢሮ እቃዎች)፣ ሎት 05 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 06 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 07 የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 08 የህትመት ውጤቶችና ቲተሮች፣ ሎት 09 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና የእጅ ዋጋ ግዥዎችን መፈጸም ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በየሎቱ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ያሳደሱ፣ በዘመኑ ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ክፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት አያይዘው ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ለሚያቀርቡ ጠቅላላ ዋጋ ድምርና ለኤሌክትሮኒክስ ነክ እቃዎች ለሆኑ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ለሁሉም ሎቶች የማይመለስ ብር 30 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል ጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ከህዳር 01/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዳር 15/2018 ዓ/ም ጨረታው በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ ህዳር 16/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በታሸገበት ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በጎ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ግዥና ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በግልጽ ይከፈታል፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ከሞሉት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከመ/ቤታችን ግዥ ፋይናንስ ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ከገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ለማስያዙ የገቢ ደረሰኝ አስቆርጦ ከሚወዳደርበት ሰነድ ጋር አብሮ ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሐሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ 2 ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ (ኮፒ) በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 እስከ ህዳር 16/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የእቃውን መጓጓዣና እንዲሁም ማናቸውም የመንግስት ታክስ ያካተተ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተኙበት በሰዓቱ ካልተገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ውድድሩ በሎት ድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ጎ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
- የሚጠግኑ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን የእጅ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ማግኙት ይችላሉ፡፡ የሚጠገኑ እቃዎች የሚጠገኑበት ቦታ ጎንደር ከተማ ወ/ፍ/ቤት በመ/ቤቱ ላሉ የስራ ሂደቶች እና ለአዘዞና ለጠዳ ንዑስ ወረዳ ፍ/ቤቶች ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጎንደር ከ/ወ/ፍ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 00 36 በመደወል መረጃ ማግኙት ይችላሉ፡፡
የጎንደር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

