ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
68

የደብረታቦር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አገልግሎት የሚዉሉ ምድብ 1 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ምድብ 2 የጽዳት እቃ፣ ምድብ 3 የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ 6000 ቴትረን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚፈለግባቸውን ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በማቅረብ ኮፒውን ከተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ከኮሌጁ ግዥ ባለሙያ ቢሮ ፊት ለፊት ከሚገኝው ሳጥን ማስገባት ይኖረባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ጠቅላላ ድምር ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የእቃውን አይነት (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ኮሌጁ ቫት ከብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ እና ዊዝሆልዲንግ ታክስ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ግብር ታክስ ሰብሳቢ ስለሆነ ቀንሶ ያስቀራል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 50 /አምሳ ብር/ ከኮለጁ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 7 በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ማግኙት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (ቢድ ቦንድ) ጨረታው ከመከፈቱ በፊት (በሲፒኦ) በጥሬ ገንዘብ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ላይ ስሙን እና አድራሽውን በመፃፍ ደብረ ታቦር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በግዥ ቢሮ ቁጥረ 1 በተዘጋጀዉ ሳጥን ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን በ16ኛዉ ቀን በ3፡00 ታሽጎ በ3፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ደረሰኝ በራሱ ስም የታተመና ተከታታይ የደረሰኝ ቁጥር ያለዉ መሆን አለበት፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 05 99 በመደወል ወይም ከኮሌጁ የግዥ ባለሙያ ቢሮ ቁጥር 1 በአካል በመገኘት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደብረታቦር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here