የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ በዋን ዋሽ ፕሮጀክት የጋሸና 1ኛ. ደረጃ ት/ቤት የመጸዳጃ ቤት እና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ግንባታ ለማሰራት በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ብር 200û000.00/ሁለት መቶ ሽህ/ እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
ለጨረታዉ የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣ በ22ኛው ቀን ይከፈታል፡፡ባይገኙም ግን በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ 2በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠ/ዋጋ 10በመቶ በተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፤በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታውን በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ለመጠየቅ በስልክ ቁጥር 0920013941 ወይም 0913835894 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት