ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
73

በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኘት ሴ/መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት በመደበኛ  በጀት ሎት 1 ጃናሞራ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ዋና ቢሮ አርክ እና የሻይ ክበብ (ሎጂ) ግንባታ በሙሉ ዋጋ  ማስገንባት፣ ሎት 2 የጃናሞራ ወረዳ አቃቢ ህግ ጽ/ቤት ለዋሰል ን/ወረዳ የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት፣ ሎት 3 የጃናሞራ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ከጃናሞራ ወረዳ ፍርድ ቤት ቅጥር ገቢ የችሎት አዳራሽ ግንባታ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፣ ሎት 4 የጃናሞራ ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት ለእ/ካብ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አንድ ብሎክ ባለ 4 መማሪያ ክፍል በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

  1. ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የህንጻ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  2. ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በህንጻ ግንባታ ሥራ ተቋራጭ የታደሰ ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ለተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ማረጋገጫቸውን ሰርተፊኬት ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. በእያንዳንዱ ሎት ግንባታው አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07  ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1.5 በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከህዳር 01/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 21/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን ህዳር 22/2018 ዓ/ም 8፡15 ታሽጎ 8፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  10. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ሲሆን ጨረታው ለ40 ተከታታይ ቀናት ፅንቶ ይቆያል፡፡
  11. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ውድቅ ይደረጋል፡፡
  12. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 /24 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here