በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ሎት1. የተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት ፣ሎት2. የሆስፒታሉን ህንጻ የሪኖሼሽን ስራ ደረጃ ስድስትና በላይ የሆኑ ተቋራጮችን ፣ሎት3. የደህንነት ካሜራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የታደስ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና በሎት ሁለት ላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸዉ።
- የግዥዉ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ኮፒከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን እና የጨረታ መመሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 3 መዉሰድ የሚቻል ሲሆን ጨረታዉ በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛዉ ቀን ድረስ እስከ 11፡30 ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት ልዩ ልዩ ምክንያት በሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ያልታገዱ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫቾች የጨረታ ሀሳባቸዉን በአማርኛ ቋንቋ ማንኛውንም የመንግስት ግብር ያካተተ ሆኖ የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጐ የድርጅቱ ክብ ማህተም ፣ፊርማ እና አድራሻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረዉ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ ) ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ሲሆን ለሎት 2 እና ለሎት 3 ግን የሞሉትን ጠቅላላ ድምር አንድ በመቶ ፤ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሆስፒታሉ የጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ገቢ በማድረግ የደረሰኙ ኦርጅናል ከፖስታው ውስጥ አብሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸዉ ከታወቀ ለተኝቶ ታካሚዎች የምግብ አቅርቦት 400‚000 (አራት መቶ ሽህ ብር) ሲሆን ለሎት ሁለት እና ለሎት ሶስት ግን ያሸነፉበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙ ግን ፕሮግራሙ የማይስተጓጎል ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የመንግስት የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ለበለጠ መረጃ 058 827 04 27 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል

