ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
112

በአብክመ ስራና ስልጠና ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያየ  መጠን  ያላቸዉ ሎት1.  የጽ/መሳሪያዎች፣ ሎት 2. የፋክስ፣ የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣ ሎት3.የፅዳት እቃዎች ፣ሎት4. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ሎት5. የቢሮ ጥገና እቃዎች፣ ሎት6. የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. አግባብነት ያለው ህጋዊ እና በዘርፉ የተሰማራ ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ  ወይም የሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ግብይቱ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በላይ ከሆነ  የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በፖስታ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው ፡፡
  5. ለኤሌክትሮኒክስ እና ለመኪና ጎማ የጨረታ ዋጋ ስትሞሉ የቴክኒካል ግምገማ ስለሚያስፈልገው ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በፖስታ በመለየት ሞልታችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
  6. ሁሉም ሎቶች ውድድሩ በሎት ስለሆነ ተወዳዳሪ ድርጅቶች ሁሉንም መሙላት ይኖርባችኋል፡፡
  7. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት በአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ ቁጥር 01 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር)  ከፍለዉ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ ።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ ሎት1. 19,000 (አስራ ዘጠኝ ሽህ ብር)፣ ሎት2 . 21,000 (ሃያ አንድ ሽህ ብር) ፣ሎት3. 13,000 (አስራ ሶስት ሽህ ብር)፣ ሎት4. 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር) ፣ሎት5. 10,000 (አስር ሽህ ብር) ፣ሎት6. 9,000 (ዘጠኝ ሽህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ  (ሲፒኦ)  ማስያዝ ይኖርባችኃል፡፡
  9.  ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ የጨረታ ሰነድ ላይ የተሞላን ዋጋ ማሻሻል ፣መለወጥ ወይም ጨረታዉን ሰርዣለሁ የሚሉት ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡
  10.  በማንኛዉም እቃ ግዥ ዋጋ ከብር 20,000 (ሃያ ሽህ ብር) ለአገልግሎት 10,000 (አስር ሽህ ብር) ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢዉ ከሚፈፀምለት ክፍያ ላይ 3በመቶ የቅድመ ግብር ክፍያ ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል።
  11.  የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛዉ ቀን ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህርዳር ከተማ በሚገኘዉ ስራና ስልጠና ቢሮ አንደኛ ፎቅ ግዥ ክፍል  ዉስጥ ይከፈታል፡፡ አስራ አምስትኛዉ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል።
  12. የጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታዉ ላይ በምታቀርቡት ሎት መሰረት በግልፅ ጨረታ የሚል በፖስታ ተፅፎበት እስከ ህዳር 16/2018 ዓ.ም መቅረብ አለበት፡፡
  13. ቢሮዉ ጨረታዉን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ስለጨረታዉ ተጨማሪ ማብራሪያ ወይም መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 222 14 34   058 226 53 97 መደወልይችላሉ፡
    የአብክመ ስራና ስልጠና ቢሮ

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here