የጨረታ ቁጥር፡-አብክመማረሚያ ቤት ኮሚሽን/ግጨ/01/2018 ዓ.ም
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የ2018 በጀት አመት ለኮሚሽንና በስሩ የሚገኙ ለዞኖችና ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል የማረሚያ ፖሊስ አባላት የደንብ ልብስ ለ4 ወር (ለተከታታይ 120 ቀናት) በሚቆይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- ሬንጀር ኮትና ሱሪ ከነመለዮው፣ ሬንጀር ሸሚዝና ሱሪ ከነመለዮው ፣የሬንጀር ቲሸርት፣ የዝናብ ልብስ ቢሮ ተመድበው ለሚሰሩ፣ ከሬንጀር ደንብ ልብስ ጋር የሚመሳሰል፣ የዝናብ ልብስ በጥበቃ ተመድበው ለሚሰሩ ከሬንጀር ደንብ ልብስ ጋር የሚመሳሰል ባለ 3 /ሶስት/ ቀዳዳ፣ 2. መደበኛ የደንብ ልብስ ሸሚዝና ሱሪ፣ መደበኛ የደንብ ልብስ ቡላማ ቲሸርት፣ የስትራቴጂክ መኮንኖች ፊልድኬፕ ፣የብሉብላክ መደበኛ ልብስ ከፍተኛ መኮንኖች ፊልድ ኬፕ፣ የብሉ ብላክ መደበኛ ልብስ የመካከለኛ መኮንኖች ፊልድ ኬፕ፣ የብሉ ብላክ መደበኛ ልብስ የዝቅተኛ ማዕረግተኞች ፊልድኬፕ፣ ብሉ ብላክ ፊልድ ጃኬት ተቋሙ በሚያቀርበዉ ከለር፣ 3. ቬሪ ቮኔት መለዮ፣ በጀርባ የሚያዝ ወታደራዊ ሚሲኖዳ፣ የስነስርአት ተቆጣጣሪ ሄልሜት፣ 4. ከቆዳ የተሰራ የመኮንኖች የወንድ ቦትና ጫማ ከነ ዚፑ፣ ከቆዳ የተሰራ የወንድ ጉርድ ጫማ፣ ከቆዳ የተሰራ የሴት ጉርድ ጫማ፣ 5. የእግር ካልሲ ረዥሙ፣ የእግር ካልሲ አጭሩ፣ 6. የተቋሙ አርማ ያለበት ጥቁር የሸራ ወታደራዊ ቀበቶ፣ የተቋሙ አርማ ያለበት ሸራ ሬንጀር ቀበቶ፣ ስሊፒንግ ባግ፣ የአልጋ አጎበር፣ 7. የፖሊስ ፊሽካ ከነዘለበቱ፣ የሱፍ ካፖርት፣ የስነሰርአት ተቆጣጣሪ ጉንጉን እና በትከሻ ላይ የሚደረግ ምልክት፣ 8 ግራንድ ዩኒፎርም የተሟላ እንዲሁም 9. የኤኬክትሮኒክስ እቃዎች እስቴሽነሪ፣ ፈርኒቸር እቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና የመኪና የዲኮር እቃዎች በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ የሚከተሉት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አምራቾች የአምራችነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ወይም ድርጅቶች አቅራቢ ከሆኑ ከአምራቹ የተሰጠ የ2017 ዓ.ም ዉክልና እና ምርቱ በትክክል የአምራቹ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ እንዲሁም አሸናፊ ከሆነ በኋላ ውል መያዝ የሚችለው በተወዳደረበት የአምራችነት ውክልና መሰረት መሆኑ ታውቆ ምርቱን ወደ አብክመ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ማስገባት የሚችለው ሲወዳደር ውክልና ከሰጠው ድርጅት ማስረጃ ሲያቀርብ ብቻ ነው፡፡
- ተጫራቾች የደንብ ልብሱን ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሌሎች እቃዎች ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 17 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ አይተም (አይነት) ማስያዝ የሚገባቸው ሲሆን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ጨረታው በባንክ በተረጋጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
የአብክመ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን

