በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ የቢሮአችን የዉስጥ እና የዉጭ የግድግዳ የቀለም ቅብ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ጋር ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፤ ከደረጃ 10 እና በላይ GC/BC፡፡
- የግብረ ክፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ የአገልግሎት ግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ገንዘብ ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በቢሮዉ ገ/ያዥ ገቢ አድርገዉ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የከተሞች መሠረተ ልማት ቢሮ ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ በ22ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ሁኖም 22ኛዉ ቀን ቅዳሜ፤ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 30 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 50 00 /058 226 61 80 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ከተሞችና መሠረተ ልማት ቢሮ

