በምሥራቅ ጎጃም ዞን የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/ አስ /ቡድን የሁለት እጁ እነሴ ወርዳ ግብርና ጽ/ቤትና ውሀ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ ማቴሪያል፣ ለሁ/እ/እ/ወ/ባቱ ጽ/ቤት አገልግለት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች እንዲሁም የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በአልማ በጀት በሞጣ ከተማ የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ግንባታ እንዲሁም የኤሌክትሪክ እቃ (ጀነሬተር) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት (ለማስገንባት) ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማለትም፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በአልማ በጀት በሞጣ ከተማ የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ግንባታ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ እና የሁለት እጁ እነሴ ወርዳ ግብርና ጽ/ቤትና ውሀ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የግንባታ ማቴሪያል ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/፣ ለሁለት እጅ እነሴ /ወ/ባቱ ጽ/ቤት አገልግለት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ከሁ/እ/እ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ከረዳት ገ/ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጥቅል ዋጋ የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በአልማ በጀት በሞጣ ከተማ የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ግንባታ ብር 120,000 /አንድ መቶ ሀያ ሽህ ብር/ የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤትና ውሀ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የግንባታ ማቴሪያል ብር 50,000/ አምሳ ሽህ ብር/ ለሁ/እ/እ/ወ/ ባቱ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችና ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ብር 5,000 /አምስት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው በጥሬ ገንዘብ የሚያስዙ ከሆነ በሁ/እ/እ/ወ ገንዘብ ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ መደረግ እና ደረሰኙ ከጨረታ ሰነዱ ጋር መያያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈፀም በተገለፀበት ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት የዕቃ /አገልግሎት ጠቅላላዋጋ 10 በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ፕሮፎርማንስ ቦንድ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ትዕዘዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank grante/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከአሸናፊው የሚቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 /ሰላሣ/ ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ ግንባታውን ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 25 በመቶ ከማህንዲሱ ግምት ዝቅ ብሎ ካሞላ
- Cost breakdown እና projeket work schedule እንዲሁም በሞላው ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ /conformation letter/ አሸናፊነት ከተገለጸ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልተው አሸናፊ ሆነው የግንባታ ተቋራጭ ውል ይዘው ወደ ሥራ ሲገቡ ቅድመ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፡፡
- የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የነበረው ተሻሽሎ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ ይሆናል፡፡
- የግንባታ የሂሳብ ስሌት በተመለከተ (አርቴሜቲክ ቸክ) በግዥ በሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- ለግንባታ ለፋይናስ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች ቢያንስ 3 እና በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ ከሂሳብ ስሌት (አርቴሚቲክ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ ተጫራቹ ከ3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት (አርቴሜቲክ ቸክ) ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ አንድ በመቶ ድረስ ብቻ ተቀባይ የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሁ/እ/እ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግንባታ ሥራዎች ለ21 ተከታታይ ቀናት እስከ 22ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ለሌሎች ግዥዎች ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ከ16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ማስገባት ለመ/ቤቱ እና ለተጫራቾች ድህንነት እንጅ እንደ መወዳደሪያ መስፈርት አይሆንም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣበት 22 ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ሌሎች ግዥዎች 16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ሰዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዥ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ውድድሩ በሎት ስለሆነ በአንድ ሎት የተቀመጡትን ዝርዝር ሙሉ በሙሉ መሙላ አለባቸው፡፡
- የእቃ ግዥዎች መ/ቤቱ ሚገዛውን እቃ 20 በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ያሸነፋቸውን እቃዎች በአሸነፋቸው ድርጅት በራሱ ወጭ መ/ቤቱ ከሚፈልግበት ቦታ ድረስ ማድረስ የሚችል መሆን አለበት፡፡ የግንባታ ሥራዎች ማቴሪያሉን እራሱ ችሎ ግንባታውን እስከሚካሄድበት ቦታ ድረስ አቅርበው መስራት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለእቃ አቅርቦት ግዥዎችን አሸናፊው ውል ይዞ እቃውን የሚያቀርበት ጊዜ በ15 ተከታታይ ቀናት ማቅረብ የሚችል፡፡ ለግንባታው በ120 /አንድ መቶ ሀያ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሰርቶ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱ 60 ተከታታይ ቀናት ጽንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ለግንባታው ስራ በጨረታው የሚሳተፍ ተጫራቾች ደረጃ 7 GC ወይም BC እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
- በተጨማሪ በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽሎ በቀረበው በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 00 /058 661 19 35 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሁለት እጅ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

