በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የደራ ወረዳ ጽ/ቤት 1ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጥገና ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ በሆኑ ተቋራጮች ማስጠገን፣ 2ኛ አንበሳሜ ከተማ ላይ ሀዉልት ለማሰራት ስለፈለገ በአርት ጋላሪ ፈቃድ ያላቸው እና በጥበብ መስክ ሀውልትና አደባባይ ፋውንቴን ግንባታ ጋር አቀናጅቶ የሰራና የመልካም ሥራ አፈፃፀም ያለውን ተቋራጭ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከላይ 1-4 ለተዘረዘሩት ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖራቸው ይገባል፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የዕቃ አቅርቦት 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ ዋጋ በመሙላት እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናል በማሸግ ከፖስታው ጀርባ ለደራ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት በማለት ስምና የሚወዳደሩበትን አይነት በመግለፅ ዘወትር በስራ ሰዓት በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሎትም ሆነ በተናጠል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 258 01 41 /09 74 08 10 74 /09 18 09 75 55 ወይም ቢሮ ቁጥር 2 በአካል በመገኘት መጠየቅ ወይም በFace book፣ ድህረ ገጻችን gera wedia Finace Office በመግባት ሙሉ መረጃውን ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

