ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
49

የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥ/ን/አስ/ቡድን  ለደደብረ ኤልያስ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት  ከ2018 መደበኛ በጀት ላይ  ከደብረ ኤልያስ – አንገታም – የሜዘኝ – ግብፃዊት እና ከግብፃዊት – የደንበኝ – ጉፍጭማ  ሜንሮድ  18.27 ኪ/ሜ አልፎ  አልፎ  መንገድ ለማስጠገን  ስለሚፈልግ ለመንገድ ጥገና አገልግሎት የሚውል ማሽን 16ሜ3 መጫን የሚችል ገልባጭ መኪና፣ ግሪደር ማሽን፣ ኤክስካቫተር፣ ሻወር ትራክ/ቦቲ/፣ ሮሎ እንዲህም ለሰርቪስ አገልግሎት የሚውል ዳብል ፒካፕ መኪና  ባለንብረቶችን በግልጽ  ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ለማሽኑ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶች ጋር አየያዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የሚጠገኑ መንገዶች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 6 ማግኝት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የሚጠገኑ መንገዶች ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ገንዘቡን በመ/ቤታችን መሂ 1  ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ ከውድድር ውጭ  ያስደርጋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን (ሰነዱን) በጥንቃቄ ያለምንም ስርዝ ድልዝ ዋጋውን በመሙላት በፖስታ አሽጎ ግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 22ኛው ቀን 2018 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 8 በ22ኛው ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የተጫራቾቸ ወይም ህጋዊ ወኪሎች አለመገኘት የጨረታ መክፈት ስርዓቱን አያስተጓጉልም፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ጨረታው ወጥቶ የሚቆየው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ይሆናል፡፡
  13. የጨረታ አሸናፊው የአሸናፊነት ደብዳቤ በተሰጠው አምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉ አምስት ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማቅረብ ከአሰሪ መስሪያ ቤቱ ጋር ውል በመያዝ ወደ ስራ መግባት አለበት፡፡
  1. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 22ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  1. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 058 250 00 10 /11 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here