በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ገንዘብ ዋና መምሪያ አንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለወረዳ ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያ እና ልዩ ልዩ የቋሚ አላቂ እቃዎች ብር 20,000 የጨረታ ማስከበሪያ፣ ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ብር 3,000 የጨረታ ማስከበሪያ፣ ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 10,000 የጨረታ ማስከበሪያ፣ ሎት 4 የህንጻ መሳሪያዎች ብር 15,000 የጨረታ ማስከበሪያ፣ ሎት 5 የመኪና ጎማ ብር 20,000 የጨረታ ማስከበሪያ፣ ሎት 6 ልዩ ልዩ የስፖርት ቁሳቁስ ብር 3,000 የጨረታ ማስከበሪያ እና ሎት 7 የውጭ ኢምፖርትድ ፈርኒቸር ብር 15,000 የጨረታ ማስከበሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚገዛው የግዥ መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባችዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ሰርተፊኬትና ቫት ሰርተፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11.30 ድረስ በስራ ስዓት የጨረታ ሰነዱን አን/ጓ/ወ/ገንዘብ/ ጽ/ቤት የክፍያ/ሂ/ማ/ደ/የሥራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 03 በማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የማወዳደሪያ ሥርዓቱ የጽህፈት መሳሪያ እና ልዩ ልዩ የቋሚ አላቂ ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የህንጻ መሳሪያዎች፣ የመኪና ጎማ፣ ልዩ ልዩ የስፖርት ቁሳቁስ እና የውጭ ሀገር ፈርኒቸር በሎት አሸናፊ የሚመረጥ ይሆናል፡፡
- የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር በሎቱ በተቀመጠው መሠረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በገንዘብ ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ መሂ-1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ አዊ ብሔ/አስ/ዞን አንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ ለ16 ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አንከሻ ወረዳ ገን/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን በቢሮ ቁጥር 08 በ16ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን (የሚከፈትበት ቀን) ብሔራዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡15 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር ይችላሉ ይሁን እንጅ የሚሞላዉ ዋጋ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር፣ የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ወጭዎች ካሉ ማካተት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃዎች አንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያ እና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 224 05 20/ 058 224 00 03 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

