የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት የሚጠቀምባቸዉ በመደበኛ በጀት የተለያዩ Anti Vius Software licence Renewal፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ እንዲሁም የተሽከርካሪ የንፅህና መጠበቂያ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ለማቅረብ የሚችሉና ህጋዊ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው አቅራቢዎች ሁሉ በጨረታዉ እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸዉ ነጥቦች እንደሚከተለዉ ተገልጸዋል፡፡ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ እና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ለሚጠይቁ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ብር ለAnti Vius Software licence Renewal ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/፣ ለየጽህፈት መሳሪያ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/፣ ለየጽዳት ዕቃ፣ ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር/ ለየተሽከርካሪ የንጽህና መጠበቂያ ብር 6,000 /ስድስት ሺህ ብር/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተመሰከረለት ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘዉ አብክመ ገቢዎች ቢሮ ቢሮ ቁጥር 313 የተለያዩ Anti Vius Software licence Renewal ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች ፣የተሽከርካሪ የንጽህና መጠበቂያዎች ለሁሉም ግዥ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ሰነዱን በመግዛት የነጠላ ዋጋ እና ጥቅል ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 313 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቅዳሜ እስከ 6:30 ጨምሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 313 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡ ስራ ስድስተኛው (16ኛዉ) ቀን ቅዳሜ ከስዓት በኋላ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰዉ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ወጭ ራሱ ችሎ ለቢሮው አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ያስረክባል፡፡
- ቢሮዉ በማንኛውም ሰዓት ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
አድራሻችን፡-ባሕር ዳር ቀበሌ 16 አብክመ ሴቶችና ህፃናት ጎን ስልክ ቁጥር 058 226 57 65 ወይም 058 226 61 71 መጠቀም ይችላሉ፡፡
የአብክመ ገቢዎች ቢሮ

