በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ጎንደር ዞን የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ/ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን መሪ አማካኝነት የ2018 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገለግሎት የሚውል ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ፣ ሎት 2 የፈርኒቸር እቃዎች፣ ሎት 3 እስቴሽነሪ፣ ሎት 4 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 5 የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አዉዳድሮ መግዛት ይፈለጋል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- ግብይቱ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባችኋል፡፡
- ከሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር አለበት ሥርዝ ድልዝ ካለው በፊርማ መረጋገጥ አለበት የሚያቀረቡት የንግድ ፈቃድና (ቲን) ግልጽና የሚነበብ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታችዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ስነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ እያንዳንዱን በደረጃ (በሎት) ተለይቶ የተዘረዘሩትን እቃዎች ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት /የግ/ን/አስ/ቡድን አማካኝነት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ህዳር 08/2018 ጀምሮ እስከ ህዳር 27/2018 ድረስ ለተከታታይ ለ21 ቀናት ይውላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት የዋጋዉን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ የሚያስይዙት ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከሆነ በአማርኛ ተተርጉም መያያዝ አለበት፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሽገ ፓስታ በማቅረብ አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት/ግ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ስዓት እስከ 22ኛው ቀን 9፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሎት የተዘረዘሩትን ጨረታዎች በ22 ኛው በቀን ህዳር 28/2018 ዓ.ም በ9፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከ10፡00 ጀምሮ ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድና ወደ ስራ መግባት አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአ/አ/ጫ/ወ/ግ/ን/አስ/ቡድን መሪ ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 97 09 /09 18 60 68 04 የሚፈልጉትን ማስረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳስቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛውም ደረጃ በነበራቸው የአፈፃፀም ችግር ምክንያት የታገዱ ወይም የእቃ አቅርቦት ችግር ያለባቸው ተጫራቾችን አይጋብዝም፡፡
የአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

