በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የደብረ ታቦር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በ2018 በጀት አመት ለመ/ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ሎት 1፣ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 2፣ የተለያዬ ህትመቶች ሎት 3፣ ቋሚ አላቂ እቃዎች ሎት 4 እና የጽዳት እቃዎች ሎት 5 በግልጽ ጨረታ የግዥ አወዳድሮ መግዛት እና በህትመት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግዥ መጠኑ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ይህ ግልጽ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛዉ ቀን ድረስ በደ/ታቦር ከ/ወ/ፍ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ በመምጣት ከዋናዉ ጋር ሊገናዘብ የሚችልና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማስረጃ በማቅረብ ለእያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም የጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በባንክ ያስያዙትን ገንዘብ (ሲፒኦ) ወይም የጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን ገቢ ያደረጉበትን የገቢ ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ አሽገዉ ደ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ብለዉ በዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን በግ/ፋ/ን/አስ ቢሮ እስከ 16ኛዉ ከቀኑ 3፡30 ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን የሚታሸገዉም በዚሁ ሰዓት ነዉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባገኙም በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ3፡45 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ የሚሆነዉ በጥቅል /በሎት/ ነዉ፡፡ ነገር ግን ከቀረቡት እቃዎች አንድም እቃ ያልሞላ ከዉድድር ወጭ ነዉ፡፡
- የሚገዙ እቃዎች ርክክቡ የሚፈፀመዉ በሙያተኛ ተረጋግጦ ነዉ፡፡
- አቅርቦት ደጎ/ዞን/ደ/ታቦር ከ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢሮ ይሆናል፡፡
- የሚገዙት እቃዎች (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መግለጫ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 141 71 78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ተቋሙ ግዥን ከቀረበዉ የዋጋ መጠን 20 በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- አሸናፊዉ የአሸነፋቸዉን እቃዎች በራሱ ወጭ በመጓጓዝ ደ/ከ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሌሎች ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ማቅረብ አይችሉም፡፡
የደብረ ታቦር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

