በምሥራቅ ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ል/ት/መምሪያ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ለሚያስገነበው G+4 የቢሮ ግንባታ በመደበኛ በጀት የጥናት እና ዲዛይን እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ዝግጅት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች
- ከላይ በተጠቀሱት የስራ ዘርፍ የሚመለከታቸውን ማስረጃዎቸ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሰራው የጥናት እና ዲዛይን እንዲሁም የጨረታ ሰነድ ዝግጅቱን የያዘ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን 11፡30 ድረስ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እስከ 31ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 የማይመለስ ብር 800 /ስምንት መቶ ብር/ በመክፈል ከዋና ገ/ያዥ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ለስራው የሚያስፈልገው የማማከር ብቃት የመሀንዲሶች አማካሪ ደረጃ 3 እና በላይ ወይም የመሀንዲሶች እና አርኪቴክቶች አማካሪ ደረጃ 3 እና በላይ ሆኖ በአማራ ክልል ከተሞች እና መሰረተ ልማት ቢሮ ወይም በፌደራል ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በኮንስትራክሽን ቁጥጥር ባለስልጣን የተረጋገጠ የእድሳት ዘመኑ ያላለፈ የሙያ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ብር 30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የአሸነፈውን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማያያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- የጫረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ እና በቴክኒክ ከፍተኛ ነጥብ የሰጠ መሆኑ ታውቆ ለሁሉም አይተሞች ዋጋ መሞላት ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ 2 ፖስታ ማለትም የቴክኒክና የፋይናሻልን የያዘ ፖስታ በደ/ጥላ/ግ/ወረዳ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት በ31ኛው ቀን 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ጀምሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለዉ ከጨረታ ዉድቅ እንደሚያደርግ አዉቀዉ በጥንቃቄ እንዲሞሉ ይደረግ፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 058 257 02 57 /01 43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት

