በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የፖሊስ ዋ/ጠ/መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ሎት1. የሰራዊት ደንብ ልብስ ፣ ሎት2. የተሸከርካሪ መለዋወጫ ፣ ሎት3. የጽህፈት መሳሪያ እና ሎት4. የጽዳት እቃዎች፣ሎት5 .የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ግዥ በነጠላ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረበዉ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚነበቡ (በደንብ የሚታይ) ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጥቃቅን እና አነስተኛ የሚወዳደሩ የንግድ ፈቃዳቸው 5 (አምስት ዓመት) ያልሞላው ለመሆኑ ከቴክኒክና ሙያ ጽ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ አለባችው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ላይ የሚገለጸውን ዋጋ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 13 ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- በሎት 1 ለተገለጸው የደንብ ልብስ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር ) ብቻ መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ፖሊስ ዋ/ጠ/መምሪያ በግዥና ፋይናንስ መምሪያ ወይም ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ተጫራቾች የተገለጸው የመኪና መለዋወጫ አሸናፊ ሆነው ውል በያዙ በ1ወር ወይም ለተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ16 ኛው ቀን 3፡30 ተዘግቶ በእለቱ ከሰዓት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡እለቱ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ፡፡
- በሎት 1 ለተገለጸው የደንብ ልብስ በእለቱ የሚዘጋ ሆኖ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለጽ ይሆናል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 21 11 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0582201453 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ

