ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

በሰሜን ወሎ ዞን በጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተሮች አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ፣ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 4  የሃገር ውስጥ ፈርኒቸር ከኤምድፍ የተሰሩ ሎት 5 የሃገር ውስጥ ፈርኒቸር ከብረት የተሰሩ፣ሎት 6 የውጭ ፈርኒቸር  በየዘርፉ ከተሰማሩ ነጋደዎች በበግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ነጋዴዎች /ድርጅቶች/ ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

  1. ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ብር 200000 (ሁለት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ አቅራቢዎች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ከቫት በፊት መሆኑን መግለጽ አለበት፡፡
  4. የሚገዙ የዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔሲፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይቻላል፡
  5. የተዘጋጀውን እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) በመክፈል ጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ በመምጣት መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ወይም ተመስርቶ መጫረት አይቻልም፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገዙበት ወቅት ናሙና ማየት ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጽ/ቤቱ ያቀረበውን ናሙና በማየት ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡ ናሙና ለቀረበበት ዕቃ በቀረበው ናሙና መሰረት የሚያቀርቡ መሆን አለበት፡፡
  8. የሚያቀርቧቸውን አቅርቦቶች (ማቴሪያሎች) የጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ባዘጋጀው የጨረታ ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የራሳቸውን ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነድ ላይ ማስቀመጥ የለባቸውም፡፡ ካደረጉም ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ላይ የአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ማስቀመጥ አለባቸው፡፡ የተሞላውን ዋጋ  ቫትን ጨምሮና  ቫትን ሳይጨምር  በማለት መግለጽ  አለባቸው፡፡
  10. ከሎት 1 አስከ ሎት 6 ያሉት ግዥዎች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች ዘወትር በስራ ስዓት እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉና የገዙትንም የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በሁለት ፖስታ በማሸግ በዚሁ የስራ ስዓት በጋ /ከ/አስ/ገ/ጽ/ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡
  11. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከረፋዱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. በጨረታው አካሄድ ቅር የተሰኘ ተጫራች ካለ ጨረታው ከተከፈተ እስከ 5 ተከታታይ ቀናት ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  13. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ አሸናፊ መሆኑ ከተገለጸ ቀን ጀምሮ አስከ 5( አምስት) ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ በጽ/ቤቱ ቀርቦ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  14. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በየሎት አይነቱ በሎት ድምር ዉጤት ሲሆን ከተዘረዘሩት እቃዎች መካከል አንዱን እንኳ አስቀርቶ ሌሎቹን መሙላት እያቻልም፡፡ ሁሉም እቃዎች መሞላት አለባቸው፡፡ ካልተሞላ ከጨረታ ወጭ ይሆናል፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  16. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድረጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ

ይጠበቅባቸዋል፡

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ሎት1. ብር 15000 (አስራ አምስት ሽህ) ፣ ሎት2. ብር 50000 ( ሃምሳ ሽህ) ብር ፣ ሎት 3 ብር 3000 ( ሶስት ሽህ)፣ ሎት4. ብር 5000 (አምስት ሽህ) ብር፣ ሎት5. ብር 2000 (ሁለት ሽህ) እና ሎት6. ብር 2000 (ሁለት ሽህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ በተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ቢያንስ ለ60 ቀናት ያህል ዋስትናው ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
  2. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠ/ዋጋ 10በመቶ በጥሬ ገንዘብ፣በተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ የውል ማስያዢያው የቆይታ ጊዜው ውሉ ከተወሰደ በኋላ ቢያንስ ለ60 ቀናት ያህል ዋስትናው ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
  3. የዕቃው ዕረክክብ የሚፈጸመውጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ሲሆን የዕቃውን ማጓጓዢያ ወጭ በአሸናፊው ( በዕቃ አቅራቢው) የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ከተገለጸው የአቅርቦት መጠን ላይ አሸናፊው የሞላው ዋጋ ሳይቀየር አቅርቦቱን 20በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ የመ/ቤቱ መብት የተጠበቀ ነው፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡

 

  1. ለበለጠ መረጃ ቢሮ ቁጥር 13 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 09 20 19 00 47 ወይም 09 95 46 22 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የጋሸና ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here