ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
55

በሰሜን ጎጃም ዞን የዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የጽህፈት መሳሪያ በግልፅ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ የእቃው ግዥ መጠን በኢትዮጵያ ብር ከ200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ  እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አያይዘው  ማቅረብአለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ድረስ በዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥፋይ/ንብ/ አስተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የዋጋ ማቅረቢያና አስፈላጊ ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ በፖስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ታትሞ ይቆይና በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/ አስተዳደር ቡድን ውስጥ ይከፈታል፡፡
  4. ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅት ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ ባይገኙም በጽ/ቤቱ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን መክፈቻ ቀኑ ማለትም በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ብር 10,000 (አስር ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በሎት ድምር ዋጋ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች በመምረጫ ሰነዱ የተዘረዘረውን ሁሉንም ዝርዝር መሙላት አለባቸው፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ወጭ ዱርቤቴ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ ቤት ድረስ አምጥቶ ገቢ ማድረግ አለበት፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  9. የሚገዙ እቃዎች (አገልግሎቶች) ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፍኬሽን) መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሠያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ ዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ግዥፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 223 08 16 09 74 50 58 99 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

የዱርበቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here