ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
72

በአብክመ በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ኃ.የተወሰነ ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ለ2018 የምርት ዘመን በተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለሚሰበስበው የተለያዩ የሰብል ምርጥ ዘር ትራንስፖርት፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሰብሰብ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ (ሲፒኦ) ከታወቀ ባንክ በጥሬው ማስያዝ የሚችሉ፡፡
  5. ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ለእያንዳንዱ የሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጉና የዘር ብዜትና ግብይት ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን በሚገኝበት ደብረ ታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ደሴት ላይ ቡና ባንክ ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የሰብል ዓይነቶችና ሰብሉ የሚሰበስብበትን ቦታ ዝርዝር መገለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶች በጥንቃቄ በፖስታ ታሽጎ ጉና ዘር ብዜትና ግብይት ኃላፊነቱ የተወሰነ ሀብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን በሚገኝበት ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደብረ ታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ደሴት ላይ ከሚገኘው ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ስዓት  ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታው ወጥቶ የሚቆይበት ጊዜ ማስታዎቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከህዳር 08/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ማለትም ህዳር 20/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ ይታሽጋል፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የመክፈቸው እለት በዓል ከሆነ ወደ በሚቀጥለው ተመሳሳይ የስራ ቀንና  ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ /ኢንቨሎፕ/ በጥንቃቄ በማሸግ የድርጅቱን ክብ ማህተም ተደርጎበት በዩኔዬኑ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ዩኔዬኑ የሚሰበስበው የተለያየ የሰብል ምርጥ ዘር የማሳ ግምት ስለሆነ ሊጨመርም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  14. ዩኔዬኑ አሸናፊውን የሚለየው በነጠላ  ዋጋ  ውጤት ሁኖ ለማወዳደር ያመች ዘንድ ሁሉም ቦታዎች አካቶ መሞላት አለባቸው፡፡ ይህም በዩኔኑ ግዥንና ሽያጭ መመሪያ መሰረት የሚፈፀም የሆናል፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ ለማግኘት 09 30 70 99 26 /09 79 26 13 56 /09 18 21 87 40 /09 18 01 85 02 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here